Вход на сайт

Просмотр новости

Найдите то, что Вас интересует

ከአሜሪካውያን ዘንድ ለእስራኤል የነበረው ድጋፍ እየቀነሰ መምጣቱ እንደሚያሳስባቸው ኔታንያሁ ገለፁ።

Дата публикации: 30-07-2026 17:05:13

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ለሀገራቸው የነበረው ድጋፍ በአሜሪካውያን ዘንድ እየቀነሰ መምጣቱ እንደሚያሳስባቸው ገለፁ።ኔታንያሁ ከዚህ ቀደም በአሜሪካና በእስራኤል መካከል ያለው ግንኙነት እንደ ግራናይት ድንጋይ ግድግዳ የጸና ቢሆንም፣ አንዳንዶች ስንጣቂ ለማግኘት የሚሞክሩ አሉ ብለው ነበር። በቅርቡ የተደረጉ የሕዝብ አስተያየት ጥናቶች በአሜሪካውያን ዘንድ ለእስራኤል የነበረው ድጋፍ መቀነሱን አመልክተዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ወደ ዋሽንግተን ያመሩት ኔታንያሁ፣ ኤቢሲ ለተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት በማኅበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ አሉታዊ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች መበርከት ለዚህ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንዳንድ መንግሥታት የተደራጀ ዘመቻ በቦት መረቦች (bot farms) ፀረ-እስራኤል አቋሞች እንደሚሰራጭ ተናግረዋል። “በእነዚህ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን መልዕክቶች መስፋፋትና ለእስራኤል ያለው ድጋፍ መቀነስ መካከል ቀጥተኛ ተያያዥነት እንዳለ እያየን ነው” ብለዋል…
The post ከአሜሪካውያን ዘንድ ለእስራኤል የነበረው ድጋፍ እየቀነሰ መምጣቱ እንደሚያሳስባቸው ኔታንያሁ ገለፁ። appeared first on Ethiopia Observer.


Основное содержимое страницы с новостью.

ከአሜሪካውያን ዘንድ ለእስራኤል የነበረው ድጋፍ እየቀነሰ መምጣቱ እንደሚያሳስባቸው ኔታንያሁ ገለፁ።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ለሀገራቸው የነበረው ድጋፍ በአሜሪካውያን ዘንድ እየቀነሰ መምጣቱ እንደሚያሳስባቸው ገለፁ።ኔታንያሁ ከዚህ ቀደም በአሜሪካና በእስራኤል መካከል ያለው ግንኙነት እንደ ግራናይት ድንጋይ ግድግዳ የጸና ቢሆንም፣ አንዳንዶች ስንጣቂ ለማግኘት የሚሞክሩ አሉ ብለው ነበር።

በቅርቡ የተደረጉ የሕዝብ አስተያየት ጥናቶች በአሜሪካውያን ዘንድ ለእስራኤል የነበረው ድጋፍ መቀነሱን አመልክተዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ወደ ዋሽንግተን ያመሩት ኔታንያሁ፣ ኤቢሲ ለተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት በማኅበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ አሉታዊ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች መበርከት ለዚህ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንዳንድ መንግሥታት የተደራጀ ዘመቻ በቦት መረቦች (bot farms) ፀረ-እስራኤል አቋሞች እንደሚሰራጭ ተናግረዋል። “በእነዚህ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን መልዕክቶች መስፋፋትና ለእስራኤል ያለው ድጋፍ መቀነስ መካከል ቀጥተኛ ተያያዥነት እንዳለ እያየን ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። “በጋዛ ያለው ጦርነት፣ እዚህ በተሳሳተ መንገድ የቀረበበት ሁኔታ እና የተሰራጩት የተሳሳቱ መረጃዎች አስተዋጽኦ አላደረጉም እያልኩ አይደለም” በማለት አክለዋል። “ለማለት እየሞከርኩ ያለሁት፣ አሜሪካን የሚጠሉ እስራኤልንም ይጠላሉ። እስራኤልን የሚጠሉ አሜሪካንን ይጠላሉ።ይህ የተከፈተብን ሰፊ ውጊያ አካል ነው” ብለዋል።

ጋዜጠኛዋ፣ የዘር ማጥፋት ጥናት ባለሙያዎችንና የተባበሩት መንግሥታትን ሪፖርቶች በመጥቀስ፣ እስራኤል በጋዛ የጦር ወንጀል መፈፀሟ አስተዋጽኦ አድርጎ ቢሆንስ ስትላቸው፣ “ይህ ሐሰት ነው ብዬ አምናለሁ።”የዘር ማጥፋት ነው” ይላሉ፤ እሺ። ግን በመጀመሪያ ይህን ክስ የሚያቀርበው ማን ነው? የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ ነው። የዘር ማጥፋት ማለት አንድን ሕዝብ ለማጥፋት ማለም፣ ይህንን ለመፈፀም ዕቅድ ማዘጋጀት እና በዚያ ዓላማ መሠረት የሚፈጸሙ ተግባራትን ያካትታል።ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የጽሑፍ መልዕክቶችንና የስልክ ጥሪዎችን በማድረግ፣ የፍልስጤም ሲቪሎች ከጉዳት አካባቢዎች እንዲርቁ አሳስበናል። በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተደብቀው የነበሩትን የሃማስ ታጣቂዎችን ለመደምሰስ እንዲቻል።የዘር ማጥፋት ዓላማ ካለን፣ ያንን ለምን አደረግን? “ሲሉ ጠይቀዋል።

ኔታንያሁ ወደ ዋሽንግተን የመጡት ባለፈው ሳምንት ሕይወታቸው ያለፈው ሪፐብሊካን የኮንግረስ አባል ሊንዚ ግርሃም ቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው። የትራምፕ የቅርብ አጋር የነበሩት የኮንግረስ አባሉ ሊንዚ ግርሃም፣ የእስራኤል ቀንደኛ ደጋፊ ነበሩ። የእስራኤሉ መሪ ከኤቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የኒው ዮርኩን ከንቲባ  ዞህራን ማምዳኒን፣  “ጥላቻ በመቀስቀስ” ወንጅለዋል።

በቃለ መጠይቁ ኔታንያሁ፣ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነት እንዲገጥሙ የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ እና በቀላሉ ድል መቀዳጀት እንደሚቻል ወስውሰዋል በሚል በተደጋጋሚ የሚቀርብባቸውን ክስ አስተባብለዋል። “ማንም ሰው ፕሬዘዳንት ትራምፕን “እንዲህ ያድርጉ” “እንዲህ አያድርጉ” የማለት አቅም ያለው የለም”ብለዋል። “እውነታው አጋሮች ነን።ወዳጆች ነን። በእርግጥ የእርሳቸው ሚና ከፍ ያለ ነው።የአሜሪካ ፕሬዘዳንት መሆናቸውን እንዳንዘነጋ።እኔ የበታቻቸው ነኝ።እኔ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ነኝ፤ የሀገሬን ጥቅምና ደህንነት ማስጠበቅ ካለብኝ ግን፤ ቅንጣት አላመነታም” ሲሉ ኔታንያሁ ተናግረዋል። ኔታንያሁ፣ ከኢራን መንግሥት ጋር በዲፕሎማሲ መፍትሔ ማግኘት ይቻላል ብለው እንደማይኑ ግን አልደበቁም። “በኢራኖች አካሄድ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ አለኝ። ሁሌም ይዋሻሉ፣ ሁሌም ያጭበረብራሉ፣ ጊዜ ለመግዛት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።ይህ በዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ጫና ሊለወጥ ይችላልን? ይሞከር።” ሲሉ ኔታንያሁ ተናግረዋል። ኔታንያሁ ደጋግሞዉ የፎከሩት የኢራንን ሥርዓት የመቀየር ወይም የኢራንን ሕዝብ በአያቶላሆቹ ሥርዓት ላይ የማሳመፅ ዕቅድ ባይሳካም፣ ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በመጠቀም በዓለም የነዳጅ ዋጋ ገበያ ላይ ጫና የማሳደር ብቃቷ እንደሚዳከም ገልጸዋል።ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመነጨውን ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ በአረብያን ፔንኑስላ አቋርጦ ወደ እስራኤል ወደቦች የሚደርሱ የነዳጅ ቧንቧዎችን በመገንባት፣ የሆርሙዝን ወሽመጥን ሳይጠቀሙ ሊጓጓዙ እንደሚችሉ፣ ይህም ኢራን በሆርሙዝ መስመሮች ላይ የበላይነት ለማግኘት የምታደርገውን ሙከራ ለመግታት እንደሚረዳ ተናግረዋል።

Схожие новости

#Наименование новостиТональностьИнформативностьДата публикации
1የእስራኤልና እና ኤምሬትስ ግንኙነት መጠናከር07.5711-07-2026
2ዮክሬን በሩሲያ መዲና ላይ ግዙፉ የድሮን ጥቃት ፈጸመች09.7713-07-2026
3Ethiopian Airlines says Eritrea has frozen ticket sale revenues05.0430-07-2026
4Ethiopian Airlines CEO says retirement due after final term extension04.7630-07-2026
5በሙስና የተጨማለቁት ዶናልድ ትራምፕ እና ቤተሰቦቻቸው010.1819-07-2026
6Газинский: сборная России в матче против шведов будет играть только на победу0019-11-2018
7В Кузнецке прошел городской конкурс «А ну-ка, парни!»0021-02-2025
8☝Мамы, хотите действительно отдохнуть и не думать как накормить любимых, ...5629-06-2026
9Агидель: Ночь 20 дек, Чт0019-12-2018
10онлайн заказ Плавание в бассейне Яндекс Маркет Задумывались ли вы ...0021-02-2025

Классификация: Международные. Схожих патентов: 0. Схожих новостей: 10. Тональность: 0. Информативность: 7.23. Источник: www.ethiopiaobserver.com.